ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ
ሴቶች ድርጅት (IEWO) እስካሁን ያከናወናቸው ሥራዎች፤
ያጋጠሙት ችግሮችና ወዴፊት ያቀዳቸው
ተግባራት
ዓለም አቀፍ
የኢትዮጵያ ሴቶች ድርጅት ሁለት ዓላማዎችን
መሠረት በማድረግ ነው የተመሠረተው::
1. ድርጅታችን
ፆታን መሠረት በማድረግ የተቋቋመ
እንዴ መሆኑ መጠን፡ የኢትዮጵያ ሴቶች
ከሚደርስባቸው ድርብ ድርብርብ ጭቆና
ነፃ እንዲወጡ ለመታገል ነው::
ሴቶች ከሚደርስባቸው
ጭቆና ነፃ መውጣት የሚችሉት ለጭቆና
የዳረጓቸው ሁኔታዎች ማለትም በቂ
የትመህርት ዕድል አለማገኘት፡ በማሀበራዊ
ሁሮም ሆነ እንደዚሁም በኢኮኖሚና
በፖለቲካ መስኮች ያላቸው ተሳትፎ
በጣም ዝቅተኛ ስለሆነ እነዚህ ሁኔታዎች
እንድለወጡ ብዙ ጥረት መደረግ እንዳለበት
ድርጅታችን ያምናል፡ ምክንያቱም
ሴቶች የማህበረሰባችን ግማሽ አካል
እንደመሆናችን መጠን ወንዶች ሊያገኙ
የሚችሉትን ዕድል እንዳገኙ ማድረግ
የጠቅላላው የህብረተሰባችን ሃላፊነት
መሆኑን በምናገኘው ሁሉ አጋጣሚ በመጠቀም
መግለፅ፡ ማሳወቅና ማንቃት እንዳለብን
በመገንዘብ ነው የሴቶች ድርጅተ እንዲቋቋም
የወሰነው::
እነዚህ
ከላይ የተጠቀሱት ሁኔታዎች የሚሟሉ
ከሆነ ለጭቆና መሠረት የሆኑት ጉዳዮች
ስለሚወገዱ ግባችንን ለመምታት እንችላለን
ማለት ነው:: ትልቁ ግባችን ሴቶች ከባህላዊ/ማህበራዊይም
ሆነ ከፖለቲካ ጭቆና ነጫ መውጣት እንዲችሉ
ከወንዶች የኢኮኖሚ ጥገኝነት ነፃ
እንዲወጡ ማድረግ ነው:: ይኸ እንግዲህ
ብዙ ጊዜ ሊወስድ የሚችል የረጅም ጊዜ
እቅዳችንና የተቋቋምንበትም ዋና
ዓላማችን ነው::
2. ሁለተኛው
ዓላማችን ደግሞ በወቅታዊው የሀገራችን
ጉዳይ የሴቶች ተሳትፎ እንዲጨምርና
እንዲጠናከር ቅስቀሳ ማድረግና ማስተማር
ነው። በአሁኑ ጊዜ ሀገራችን ከባድ
የኢኮኖሚ፡ የፖለቲካና የማህበራዊ
ኑሮ ቀውስ ውስጥ ስለወደቀች እኛ ሴቶች
ከዳር ሆነን የምንመለከተው ጉዳይ
ሊሆን ስለማይገባ፡ በዋናነት ትኩረት
ሰጥተን አብዛኛውን ጊዜአችን የምናጠፋው
በሀገራችን ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በመወያየት
ነው:: ስለዚህም ብዙ ሴቶች በሀገራችን
ጉዳይ ላይ እንዲሳተፉ ብዙ የማንቃትና
የቅስቀሳ ተግባሮች ወከናወን አለባቸው
ብለን እናምናለን:: በሀገራችን የተነሰራፋውን
ዘረኛና ፀረ ኢትዮጵያ ሥርዓት ለማስወገድ
እንዲቻል ሴቱም ወንዱም፤ ትንሹም
ትልቁም ባጠቃላይ ሁላችንም አበረን
መሥራት አለብን ምክንያቱም ሴቶች
በትጋት ያልተሳተፉበት ትግል ግቡን
ሊመታ አይችልም። ስለሆነም የሴቶችን
ሚና ኢትዮጵያዊያን ወንድሞቻችን
እንደ ቀላል ጉዳይ እንደማያዩት እርግጠኞች
ነን::
ስለዚህም
ሀገራችን ከገባችበት ከባድ አጣብቂኝ
ውስጥ እስከምትወጣ ድረስ እኛ ሴቶች
የሴቶችን ጉዳይ ማለትም ፆታን መሠረት
ያደረገ ጭቆናን ወደ ጎን በመተው ከወንድሞቻችን
ጋራ በመሆን ሀገራችንን ከወያኔ የጥፋት
ተልዕኮ ለማዳን የሚቻለውን ሁሉ እናደርጋለን።
ይኸ ሲባል ግን የድርጅት ነፃነታችንን
እናጣለን ወይንም አሳልፈን ለሌላ
ድርጅት እንሰጣለን ወይንም የፖለቲካ
ሀይሎች መጠቀሚያ እንሆናለን ማለት
አይደለም:: ድርጅታችን ከማንኛውም
የፖለቲካ ቡድን ተፅኖ ውጭ እንዲሆን
ነው ፍላጎታችን፤ ምክንያቱም ይኸ
ዓይነቱ የጥገኝነት አካሄድ በሁዋላ
እንድሟላልን ለምንፈልገው የፆታ
እኩልነትና በሀገራችን እውን እንድሆንልን
ለምንሻው ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ
ትልቅ እንቅፋት ሰለሚሆን ነው:: ጠንካራ
ሲቢክ ድርጅቶች ወይንም ማህበራዊ
ስብስቦች ለዲሞክራሲ ግንባታ የመሠረት
ድንጋዮች ናቸው ብለን እናምናለን::
በርግጥም በሀገራችን ዲሞከራሲ እንዲሠራ
ከተፈለገ ሁላችንም ይኸንን መርህ
መቀበል ያለብን ይመስለኛል::
ድርጅታችን እሰካሁን
ያከናዎናቸው ተግባራተ
ድርጅታችን ከተመሠረተ
ጀምሮ ካከናዎናቸው ተግባራት ዋና
ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸወ፦
1.
የራሱን
ድረ ገጽ (Website) በማዘጋጀት ራሱን በስፋት
በማስተዋወቅ ላይ ከመሆኑም በላይ
አንዳንድ አገራዊ የሆኑ አንገብጋቢ
ጉዳዮች ላይ ጽሁፎችን በማውጣት ውይይት
እንድደረግባቸው ጥረት እያደረገ
ነው::
2.
ከቅርብ
ጊዜ ወዲህ ደግሞ በፓልቶክ ክፍላችን
(ቴክኖሎጂ የፈጠረውን ሁሉ አጋጣሚ
በመጠቀም) ስለ ሀገራችን ወቅታዊ ጉዳዮችና
ስለ ሴቶች ችግርና በሀገራችን ፖለቲካ
ውስጥ ስለነበራቸው ታሪካዊ ቦታ፡
እንደዚሁም ሀገራችንን ከጠላት ወረራ
ለመከላከል ስለከፈሉት መስዋዕትነት
ወንዶች ኢትዮጵያዊያን በተለይም
የተምክተኝነት ስሜት ያላቸው እንዲያውቁት
ለማድረግ ጥረት እያደረግን ነው::
3.
ባለፉት
አምስት ወራት ደግሞ ቦይኮት ወያኔ
(Boycott Woyane ) በሚል ርዕስ በወያኔ መንግሥት
አማካይነት ወይንም የሥርዓቱ ተባባሪ
በሆኑ ግለሰቦች ከኢትዮጵያ እያመጡ
የሚሽጧቸውን የምግብ ሸቀጦች በተለይም
እንጀራ ማንም እንዳይገዛ ቅስቀሳ
ስናደርግ ቆይተናል:: በሀገራችን ከባድ
የምግብ እጥረት እንዳለ እየታወቀ
ከኢትዮጵያ ለሽያጭ (ለንግድ) ወደ ውጭ
የሚላኩ የምግብ ሸቀጦችን መግዛት
ማለት ከተራቡ ህፃናቶች አፍ ነጥቆ
እንደ መብላት የሚቆጠር መሆኑን በመደጋገም
በሬዲዮአችን፤ በድረ ገጻችንና እንደዚሁም
በፓልቶክ ክፍላችን አሳውቀናል፤
አሁንም በትጋት እየሠራንበት ያለ
ጉዳይ ነው;; የቦይኮት ወያኔ እንቅስቃሴአችንም
ተፈላጊውን ውጤት እያመጣ ነው:: ብዙ
ኢትዮጵያዊያን የወያኔን ሸቀጦች
በተለይም እንጀራ ቦይኮት እንዳደረጉ
ለማወቅ ችለናል:: ሆኖም ግን በዚህ ሥራ
ላይ ገና በውጭ የሚኖረውን አብዛኛውን
ህበረተሰባችንን የማንቃትና የቅስቀሳ
ተግባሮች እንደሚጠብቁን እንረዳለን::
የቦይኮት ወያኔ
እንቅስቃሴአችን ቀስ በቀስ በዜና
ማሰራጫዎች ሁሉ እየተሰማ ስለሆነ
ተፈላጊውን ግብ ሊመታ እንደሚችል
ተስፋ አለን:: በቦይኮትም ሆነ በማንኛውም
በሚያመቸን መንገደ ለመንቀሳቀስ
የወሰንበት ምክንያት የህዝባችንን
የነፃነት ተስፋ ያጨለመውና የሀገራችንን
ህልውና አደጋ ላይ የጣለው የወያኔ
መንግሥት በማንኛውም የትግል ዘዴ
መዳከምና በጉልበት ከያዘው ሥልጣን
መወገድ አለበት ብለን ስለምናምን
ነው::
ወዴፊት ለማድረግ
ያቀድናቸው ተግባራት
- የተጀመረውን
የቦይኮት ወያኔ እንቅስቃሴ በብዙ
አቅጣጫ ማለትም
በኢኮኖሚ፤ በማህበራዊ ኑሮና
በፖለቲካ ዘርፎች ዘረኛው መንግሥት
ተንኮታኩቶ እስከሚወድቅና ሥልጣን
ለኢትዮጵያ ህዝብ እስከሚያስረክብ
ድረስ ይቀጥላል::
- የሴቶች
ተሳትፎ እንዲሰፋና እንዲጠነክር
ብዙ ሴቶች አባሎቻችን እንድሆኑና
ለምናደርገው ጣምራ ትግል የበኩላቸውን
አስተዋፅኦ እንዳደርጉ የምንችለውን
ሁሉ እንቅስቃሴ እናካሂዳለን:: የኢትዮጵያ
ሴቶች በሀገራቸው ጉዳይ ላይ
ከኢትዮጵያውያን
ወንዶች ጋራ በመሰለፍ ይኸንን አስከፊ
ሥርዓት ለማስወገድ በሚደረገው ትግል
ሙሉ ተሳትፎ እንዳደርጉ ብዙ የቅስቀሳና
የማንቃት እንቅስቃሴዎች መሥራት
እነዳለብን እንረዳለን:: ፖለቲካ የወንዶች
ሥራ ነው የሚለው አጉል እምነት መወገድ
አለበት ሴቶች ከፆታ ጭቆና ነፃ መውጣት
እንድችሉ::
- ሀገራችን
ከገባችበት ሁለገብ ቀውስ ውስጥ ለመውጣት
እንዲትችል አብረው መሥራት የሚችሉና
ወያኔን ለማስወገድና ኢትዮጵያን/ኢተዮጵያዊነትን
ለመታደግ፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ተጨባጭ
የፖለቲካ እንቅስቃሴ የሚያደርጉትን
ሀይሎች ሁሉ ለማገዝ ድርጅታችን የሚችለውን
ሁሉ ድጋፍ ያደርጋል:
ለኛ
ድርጅትም ሆነ ለቀሩት በተለያየ መንገድ
ለተደራጁት የፖለቲካም ሆነ የሲቪክ
ድርጅቶች የህልውናችን መሠረትና
የኛነታችን መግለጫ ሀገራችን ኢትዮጵያ
ስለሆነች ኢትዮጵያችንን ከወያኔ
ምንደኞች ለማላቀቅና ነፃና ዲሞክራሲያዊት
ኢትዮጵያን ለመመሥረት እንድንችል
ያሉንን ጥቃቅን ልዩነቶች ወደ ጎን
በመተው አንድነታችንን እንድናጠናክር
በዚሁ አጋጣሚ ለሁሉሙ ኢትዮጵያውያን
ጥሪ እናቀርባለን::
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ
ኢትዮጵያ በነፃነቷ
ኮርታ ለዘላለም ትኖራለች::
Prepared by Empress Candace